ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤
መሳፍንት 9:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዕለታት አንድ ቀን ዛፎች የሚያነግሡትን ለመቀባት ወጡ፤ ወይራንም፥ “አንተ ንጉሣችን ሁን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዕለታት አንድ ቀን ዛፎች የሚያነግሡትን ለመቀባት ወጡ፤ ወይራንም፣ ‘አንተ ንጉሣችን ሁን’ አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕለታት አንድ ቀን ዛፎች ተሰብስበው በላያቸው ንጉሥ ሊያነግሡ ሄዱ፤ የወይራንም ዛፍ ‘በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ጊዜ ዛፎች በላያቸው ንጉሥ ሊያነግሡ ሄዱ፤ ወይራንም፦ በእኛ ላይ ንገሺልን አሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ጊዜ ዛፎች በላያቸው ንጉሥ ሊያነግሡ ጌዱ፥ ወይራውንም፦ በእኛ ላይ ንገሥ አሉት። |
ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮስያስ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ እንዲህ ብሎ ላከ፦ “የሊባኖስ ኩርንችት፦ ‘ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው’ ብሎ ወድ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኩርንችቱን ረገጠ።
ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፥ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምጽን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ የሴኬም ነዋሪዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ፤