መሳፍንት 9:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱ የሴኬም ሕዝብ ወደ ዕርሻ ወጡ፤ ይህም ለአቤሜሌክ ተነገረው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም የሴኬም ሕዝብ ወደ ዕርሻ ወጡ፤ ይህም ለአቢሜሌክ ተነገረው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ የሴኬም ሕዝብ ወደየእርሻቸው መሄዳቸውን አቤሜሌክ ሰማ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ሕዝቡ ወደ እርሻ ወጡ፤ ለአቤሜሌክም ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ሕዝቡ ወደ እርሻ ወጡ፥ አቤሜሌክም ሰማ። |
እርሱም ሰዎቹን አስከትሎ ወጣ፤ ከዚያም ሰዎቹን ሦስት ቦታ መድቦ በዕርሻዎቹ ውስጥ አድፍጠው እንዲጠባበቁ አደረገ። አቤሜሌክ የሴኬም ሰዎች ከከተማይቱ መውጣታቸውን እንዳየም ካደፈጠበት ሊወጋቸው ተነሣ።