መሳፍንት 9:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንግዲህ አቤሜሌክን ስታነግሡት በቅንነትና በእውነት አድርጋችሁት ከሆነ፥ ይሩበኣልንና ቤተሰቡን በበጎ ዐይን ተመልክታችሁ ላደረገው የሚገባውን አይታችሁለት ከሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ አቢሜሌክን ስታነግሡት በእውነትና ያለ እንከን አድርጋችሁት ከሆነ፣ ይሩባኣልንና ቤተ ሰቡን በበጎ ዐይን ተመልክታችሁ ላደረገው የሚገባውን አይታችሁለት ከሆነ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአታምም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አላቸው፤ “አቤሜሌክን ስታነግሡ በቅንነትና ተገቢ በሆነ መንገድ ነውን? ጌዴዎን ያደረገውን በማስታወስ ቤተሰቡን እንደሚገባ ረዳችሁለትን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን እንግዲህ አቤሜሌክን በማንገሣችሁ እውነትንና ቅንነትን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ ለይሩበኣልም፥ ለቤቱም በጎ አድርጋችሁ እንደሆነና እንደ እጁም ዋጋ መጠን ለእርሱ የተገባውን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እንግዲህ አቤሜሌክን በማንገሣችሁ እውነትንና ቅንነትን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ ለይሩበኣልም ለቤቱም በጎ አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ እንዳደረገውም መጠን ለእርሱ የተገባውን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ |
የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።