መሳፍንት 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለስ ግን፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ እጅግ ጣፋጭና መልካም የሆነውን ፍሬዬን መስጠት ልተውን?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በለስ ግን፣ ‘ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፣ እጅግ ጣፋጭና መልካም የሆነውን ፍሬዬን መስጠት ልተውን?’ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበለስ ዛፍ ግን ‘ጣፋጭና መልካም ፍሬዬን መስጠት ትቼ በዛፎች ላይ ለመንገሥ ልሂድን?’ አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለሷ ግን፦ ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ በዛፎች ላይ እነግሥ ዘንድ ልሂድን? አለቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በለሱ ግን፦ ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ በዛፎች ላይ እንድሰፍፍ ልሂድ? አላቸው። |