ከዚህ በኋላ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በሐሬስ ዳገት በኩል ከጦርነቱ ተመለሰ፤
ከዚህ በኋላ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በሐሬስ መተላለፊያ በኩል አድርጎ ከጦርነቱ ተመለሰ፤
የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በሔሬስ ዳገት በኩል ከጦርነት ተመለሰ፤
የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎንም ከአሬስ ዳገት ከጦርነት ተመለሰ።
የኢዮአስ ልጅም ጌዴዎን ከሔሬስ ዳገት ከሰልፍ ተመለሰ።
ሁለቱ የምድያም ነገሥታት ዛብሄልና ጻልሙና ሸሹ፤ ጌዴዎን ግን አሳዶ ያዛቸው፤ መላ ሠራዊታቸውንም እጅግ በታተነው።
እርሱም የሱኮት ሰው የሆነ አንድ ወጣት ማረከ፤ መረመረውም፤ ወጣቱም የሰባ ሰባት የሱኮት ሹማምንትና የከተማይቱንም አለቆች ስም ጻፈለት።