La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 6:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፤ የበግ ጠጉር ባዘቶ በአውድማው ላይ አኖራለሁ። ምድሩ በሙሉ ደረቅ ሆኖ ባዝቶው ላይ ብቻ ጤዛ ቢኖር፥ እንዳልከው እስራኤላውያንን በእኔ እጅ እንደምታድናቸው አውቃለሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ የበግ ጠጕር ባዘቶ በዐውድማው ላይ አኖራለሁ። ምድሩ በሙሉ ደረቅ ሆኖ ባዘቶው ላይ ብቻ ጤዛ ቢኖር፣ እንዳልኸው እስራኤላውያንን በእኔ እጅ እንደምታድናቸው ዐውቃለሁ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነሆ! ስንዴ በምንወቃበት አውድማ ላይ የተባዘተ የበግ ጠጒር አስቀምጣለሁ፤ ነገ ጧት ሌላው ምድር ሁሉ ደረቅ ሆኖ በዚህ ጠጒር ባዘቶ ላይ ብቻ ጤዛ ከሆነ፥ እንደ ተናገርከው እስራኤልን ለማዳን የመረጥከኝ መሆኑን አረጋግጣለሁ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ! በዐ​ው​ድ​ማዉ ላይ የተ​ባ​ዘተ የበግ ጠጕር አኖ​ራ​ለሁ፤ በጠ​ጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በም​ድ​ሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተና​ገ​ርህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእኔ እጅ እን​ደ​ም​ታ​ድ​ና​ቸው አው​ቃ​ለሁ” አለ።

Ver Capítulo



መሳፍንት 6:37
11 Referencias Cruzadas  

ውኃ እጠጣ ዘንድ እንስራሽን አዘንብዪ የምላት እርሷም አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ የምትለኝ ቆንጆ፥ እርሷ ለባርያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፥ በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”


እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይውረድ።


ቁጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ከዳተኝነታቸውን እፈውሳለሁ፥ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ።


እርሱም “የተላክሁት ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች ነው እንጂ ለሌላ አይደለም” ሲል መለሰ።


ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬ እንደ ጠል ይንጠባጠብ፤ በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ በሣርም ላይ እንደ ካፊያ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ዝናብ፥


ጌዴዎን እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “አሁን በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ በእርግጥ የምታነጋግረኝ አንተ ራስህ ለመሆንህ ምልክት ስጠኝ፤


ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “በተናገርኸው መሠረት እስራኤላውያንን በእጄ የምታድናቸው ከሆነ፥


እንደዚሁም ሆነ፤ ጌዴዎን በማግስቱ ጠዋት ማልዶ ተነሣ፤ ባዘቶውንም ሲጨምቅ የወጣው ውሃ አንድ ቆሬ ሞላ።