እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።
መሳፍንት 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም፥ “በእርግጥ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ምድያማውያንንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታቸዋለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም፣ “በርግጥ እኔ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ምድያማውያንንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታቸዋለህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “እኔ ስለምረዳህ ይህን ማድረግ ትችላለህ፤ ምድያማውያንንም እንደ አንድ ሰው ያኽል አድርገህ ታደቃቸዋለህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ታጠፋለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፦ በእርግጥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ አለው። |
እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።
ከዚያም ደቀመዛሙርቱ ወጥተው፥ በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ ትምህርታቸውንም ተከትለው በሚፈጸሙ ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።
“ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ ጌታ ከአንተ ጋር ነውና፥ ጠላቶችህን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄድ፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ከአንተ የሚበልጥ ሠራዊትንም በምታይበት ጊዜ አትፍራቸው።
ጌታ መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ ከመስፍኑ ጋር ስለሚሆን፥ እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ጌታ ከጠላቶቻቸው ያድናቸው ነበር፤ ከጠላቶቻቸው ሥቃይና መከራ ሲደርስባቸው በሚጮኹበት ጊዜ ጌታ ይራራላቸው ነበር።
ከጥቂት ጊዜ በኋላም፥ ቦዔዝ ከቤተልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው። እነርሱም፦ “ጌታ ይባርክህ” ብለው መለሱለት።