በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቆሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።
መሳፍንት 5:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመስኮት ሆና ተመለከተች፥ የሲሣራ እናት በሰቅሰቅ ዘልቃ፦ “ስለምን ለመምጣት ሠረገላው ዘገየ? ስለ ምንስ የሠረገላው መንኰራኵር ቈየ?” ብላ ጮኸች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤ ‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ? የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በዐይነ ርግብ ቀዳዳም አተኲራ አየች፤ “የልጄ ሠረገላ ለምን ዘገየ? የሠረገላዎቹ ፈረሶች የኮቴ ድምፅስ ለምን ዘገየ?” ስትል ጠየቀች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በሰቅሰቅም ዘልቃ፦ ከሲሣራ የተመለሰ እንዳለ አየች፤ ስለምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመስኮት ሆና ተመለከተች፥ የሲሣራ እናት በሰቅሰቅ ዘልቃ፦ ስለ ምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለ ምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች። |
በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቆሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፥ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ።
ጌታም ሲሣራንና ሠረገሎቹን ሁሉ በባራቅ ፊት በሰይፍ ስለት እጅግ ተሸንፈው ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ አደረገ፤ ሲሣራም ከሠረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።