መሳፍንት 3:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ሞዓብ በእስራኤል ድል ሆነች፤ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ሰላም አገኘች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ሞዓብ በእስራኤል ድል ሆነች፤ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ሰላም አገኘች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን ሞአባውያን በእስራኤላውያን ድል ተመቱ፤ በምድሪቱም ላይ ሰማኒያ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት ሞዓባውያን በእስራኤል እጅ ገቡ፤ ምድሪቱም ሰማንያ ዓመት ዐረፈች። ናዖድም እስኪሞት ድረስ ገዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ሞዓብ ከእስራኤል እጅ በታች ተዋረደ፥ ምድሪቱም ሰማንያ ዓመት ዐረፈች። |
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።
የሰውዬው ስም ኤሊሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ናዖሚ፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ እነርሱም የቤተልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ፥ በዚያም ተቀመጡ።