መሳፍንት 3:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ብርቱና ይለኛ የሆኑ ዐሥር ሺህ ሞዓባውያንን ገደሉ፤ አንድም ሰውአላመለጠም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ብርቱና ኀይለኛ የሆኑ ዐሥር ሺሕ ሞዓባውያንን ገደሉ፤ አንድም ሰው አላመለጠም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን ብቻ ወደ ዐሥር ሺህ የሚያኽሉ ምርጥ የሆኑ የሞአባውያን ወታደሮችን ገደሉ፤ ከእነርሱ መካከል ማንም ያመለጠ አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት ከሞዓብ ዐሥር ሺህ የሚያህሉትን፥ ጐልማሶችና ጽኑዓን ሁሉ ገደሉ፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ አላመለጠም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያን ጊዜም ከሞዓብ አሥር ሺህ የሚያህሉትን፥ ጎልማሶችና ጽኑዓን ሁሉ፥ መቱ፥ አንድ እንኳ አላመለጠም። |
በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።
እርሱም “ጠላታችሁን ሞዓብን ጌታ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ተከተሉኝ” በማለት አዘዛቸው፤ እነርሱም ተከትለውት ወረዱ፤ ከዚያም ከዮርዳኖስ ወደ ሞዓብ የሚያሻግሩትን ስፍራዎች በመያዝ አንድም ሰው እንዳያልፍ ከለከሉ።