መሳፍንት 3:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ኤሁድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታ ይም አመለጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ናዖድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታይም አመለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እዚያው ቆመው በሚጠባበቁበት ጊዜ ኤሁድ ርቆ ሄዶ ነበር፤ ተጠርበው የተተከሉ የጣዖት ድንጋዮችን አልፎ ወደ ሰዒራ አመለጠ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከሚታወኩም ድረስ ናዖድ አመለጠ፤ ያወቀውም የለም፤ ከጣዖቶቻቸውም አልፎ ወደ ሴይሮታ አመለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዘገዩበትም ጊዜያት ናዖድ ሸሸ፥ ትክል ድንጋዮቹንም አለፈ፥ ወደ ሴይሮታም አመለጠ። |
ኤልዛቤል የመቀበር ዕድል እንኳ አታገኝም፤ የእርሷም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤’” ይህን ሁሉ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወጣቱ ነቢይ በሩን በመክፈት ከዚያ ክፍል ወጥቶ ሸሸ።
እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የእልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቊልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፥ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት።