ፀሐይ ልትጠልቅ ጥቂት ሲቀራትም “እያንዳንዱ ሰው ወደየአገሩና ወደየከተማው ተመልሶ ይሂድ!” የሚል ትእዛዝ ከእስራኤል ጦር አዛዦች ተነገረ።
መሳፍንት 21:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ያን ቦታ ትተው ወደየቤታቸው፥ ወደየርስታቸው፥ ወደየጐሣቸውና ወደየነገዳቸው ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ እስራኤላውያን ያን ቦታ ትተው ወደ የቤታቸው፣ ወደየርስታቸው፣ ወደየጐሣቸውና ወደየነገዳቸው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ጊዜ ሌሎቹም እስራኤላውያን በሙሉ ለመሄድ ተነሡ፤ እያንዳንዱም ወደ ራሱ ነገድና ቤተሰብ እንዲሁም ወደራሱ ቤት ንብረት ተመለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም የእስራኤል ልጆች ከዚያ ተነሡ፤ እያንዳንዱም ወደ ወገኑና ወደ ነገዱ ሄደ፤ ሰውም ሁሉ ከዚያ ወደ ርስቱ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም የእስራኤል ልጆች ከዚያ ተነሡ፥ እያንዳንዱም ወደ ነገዱና ወደ ወገኑ ሄደ፥ ሰውም ሁሉ ከዚያ ወደ ርስቱ ተመለሰ። |
ፀሐይ ልትጠልቅ ጥቂት ሲቀራትም “እያንዳንዱ ሰው ወደየአገሩና ወደየከተማው ተመልሶ ይሂድ!” የሚል ትእዛዝ ከእስራኤል ጦር አዛዦች ተነገረ።
ብንያማውያን እንደ ተባሉት አደረጉ፤ ልጃገረዶቹ በሚጨፍሩበትም ጊዜ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እየጠለፈ ሚስት እንድትሆነው ይዞ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ርስታቸው ተመለሱ፤ ከተሞቻቸውንም አድሰው በዚያ ኖሩ።