ከዚያም እስራኤላውያን ወደ ብንያም ምድር ተመልሰው ከተሞቻቸውን በሙሉ እንዲሁም እንስሳቱንና በዚያ ያገኙትን ሁሉ በሰይፍ መቱ፤ በመንገዳቸው ያገኙትን ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ።
መሳፍንት 21:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብንያማውያን እንደ ተባሉት አደረጉ፤ ልጃገረዶቹ በሚጨፍሩበትም ጊዜ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እየጠለፈ ሚስት እንድትሆነው ይዞ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ርስታቸው ተመለሱ፤ ከተሞቻቸውንም አድሰው በዚያ ኖሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብንያማውያን እንደ ተባሉት አደረጉ፤ ልጃገረዶቹ በሚጨፍሩበትም ጊዜ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እየጠለፈ ሚስት እንድትሆነው ይዞ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ርስታቸው ተመለሱ፤ ከተሞቻቸውንም አድሰው በዚያ ኖሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብንያማውያንም እንደዚሁ አደረጉ፤ በብዛታቸው ልክ እያንዳንዱ በሴሎ ከሚጨፍሩት ልጃገረዶች መካከል እየጠለፈ በሚስትነት ይዞ ሄደ፤ ወደ ግዛታቸውም ተመልሰው ከተሞቻቸውን በማደስ በዚያ ኖሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ በቍጥራቸውም መጠን ከተነጠቁት ዘፋኞች ሚስትን ወሰዱ፤ ወደ ርስታቸውም ተመልሰው ሄዱ፤ ከተሞችንም ሠርተው ተቀመጡባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፥ በቁጥራቸውም መጠን ከተነጠቁት ዘፋኞች ሚስት ወሰዱ፥ ወደ ርስታቸውም ተመልሰው ሄዱ፥ ከተሞችንም ሠርተው ተቀመጡባቸው። |
ከዚያም እስራኤላውያን ወደ ብንያም ምድር ተመልሰው ከተሞቻቸውን በሙሉ እንዲሁም እንስሳቱንና በዚያ ያገኙትን ሁሉ በሰይፍ መቱ፤ በመንገዳቸው ያገኙትን ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ።