ብንያማውያንም ከመላው የጊብዓ ነዋሪዎች መካከል ከተመረጡት ሰባት መቶ ሰዎች ሌላ፥ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ስድስት ሺህ ሰዎች በአንድ አፍታ ከየከተሞቻቸው በተጨማሪ አሰባሰቡ።
መሳፍንት 20:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ዕለት ሰይፍ የታጠቊ ሃያ አምስት ሺህ ብንያማውያን በጦር ሜዳ ወደቊ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ዐምስት ሺሕ ብንያማውያን በጦር ሜዳ ወደቁ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን በአጠቃላይ የተገደሉት ብንያማውያን ኻያ አምስት ሺህ ሲሆኑ ሁሉም ምርጥ ጦረኞች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም በዚያ ቀን ከብንያም የሞቱት ሃያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም በዚያ ቀን ከብንያም የሞቱት ሀያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፥ እነዚህ ሁሉ ጽኑዓን ነበሩ። |
ብንያማውያንም ከመላው የጊብዓ ነዋሪዎች መካከል ከተመረጡት ሰባት መቶ ሰዎች ሌላ፥ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ስድስት ሺህ ሰዎች በአንድ አፍታ ከየከተሞቻቸው በተጨማሪ አሰባሰቡ።
ጌታም ብንያምን በእስራኤል ፊት መታው፤ በዚያችም ዕለት እስራኤላውያን በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ብንያማውያንን ገደሉ።
ብንያማውያን ወደ ሁላ ዙረው በምድረ በዳው በኩል ወደ ሬሞን ዐለት በሚሸሹበት ጊዜ፥ እስራኤላውያን በመንገድ ላይ አምስት ሺህ ሰው ገደሉባቸው፤ እስከ ጊድኦምም ድረስ ተከታትለው ሁለት ሺህ ሰዎች በተጨማሪ ገደሉ።
ሳኦልም፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።