መሳፍንት 20:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያንም ወዲያውኑ እንዲያፈገፍጉ ነበር። ብንያማውያንን ማጥቃት እንደ ጀመሩ፥ ሠላሳ እስራኤላውያንን ስለ ገደሉ፥ “እንደ መጀመሪያው የጦርነት ጊዜ እያሸነፍናቸው ነው” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም ይህን ሲያዩ ወዲያውኑ እንዲያፈገፍጉ ተስማሙ። ብንያማውያንን ማጥቃት እንደ ጀመሩ፣ ሠላሳ እስራኤላውያንን ስለ ገደሉ፣ “እንደ መጀመሪያው የጦርነት ጊዜ እያሸነፍናቸው ነው” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምልክቱም መሠረት በጦር ሜዳ የነበሩት እስራኤላውያን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ይወስዳሉ፤ እስከ አሁን ብንያማውያን ሠላሳ እስራኤላውያንን በመግደላቸው “ከዚህ በፊት እንዳደረግነው አሁንም ፈጀናቸው!” እያሉ ይደነፉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም አርበኞች ከሰልፉ ተመለሱ፤ ብንያማውያንም እንደ ቀድሞው ሰልፍ በፊታችን ተመትተዋል እያሉ ከእስራኤል ሰዎች ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎችን መምታትና መግደል ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ከሰልፉ አፈገፈጉ፥ ብንያማውያንም፦ እንደ ቀድሞው ሰልፍ በፊታችን ተመትተዋል እያሉ ከእስራኤል ሰዎች ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎች መምታትና መግደል ጀመሩ። |
ብንያማውያኑ፥ “እንደ በፊቱ ይሄው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፥ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፥ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማይቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር።