La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 20:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብንያማውያኑ፥ “እንደ በፊቱ ይሄው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፥ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፥ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማይቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ብንያማውያኑ፣ “እንደ በፊቱ ይኸው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፣ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፣ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማዪቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ብንያማውያንም “ልክ ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ፈጀናቸው” አሉ። እስራኤላውያን ግን “ወደ ኋላ አፈግፍገን ከከተማው ወደ አውራ ጐዳናው እናስወጣቸው” አሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የብ​ን​ያ​ምም ልጆች፥ “እንደ ቀድ​ሞው በፊ​ታ​ችን ይሞ​ታሉ” አሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን፥ “እን​ሽሽ፤ ከከ​ተ​ማም ወደ መን​ገድ እና​ር​ቃ​ቸው” አሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የብንያምም ልጆች፦ እንደ ቀድሞው በፊታችን ተመቱ አሉ። የእስራኤል ልጆች ግን፦ እንሽሽ፥ ከከተማም ወደ መንገድ እንሳባቸው አሉ።

Ver Capítulo



መሳፍንት 20:32
6 Referencias Cruzadas  

እኔ ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማይቱ እንቀርባለን፤ እኛንም ሊገናኙ እንደ ፊተኛው በወጡ ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን፤


እነርሱም፦ ‘እንደ ቀድሞው ከእኛ ዘንድ እየሸሹ ናቸው’ ይላሉና ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል፤ እኛም ከፊታቸው እንሸሻለን።


ብንያማውያንም ሊገጥሟቸው ወጡ፤ ከከተማይቱም ርቀው እንዲሄዱ ተደረጉ፤ እንደ በፊቱም እስራኤላውያንን ይገድሉ ጀመር። ከዚህ የተነሣም በሜዳው እንዲሁም ወደ ቤቴልና ወደ ጊብዓ በሚወስደው መንገዶች ላይ ሠላሳ ያህል ሰዎች ወድቀው ነበር።


የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ከነበሩበት ቦታ አፈግፍገው በበኣልታማር ስፍራ ስፍራቸውን ያዙ። ሸምቆ ይጠባበቅ የነበረው የእስራኤል ጦር ደግሞ ካደፈጠበት ከጊብዓ በስተ ምዕራብ ካለው ቦታ ወጣ።


እስራኤላውያንም ወዲያውኑ እንዲያፈገፍጉ ነበር። ብንያማውያንን ማጥቃት እንደ ጀመሩ፥ ሠላሳ እስራኤላውያንን ስለ ገደሉ፥ “እንደ መጀመሪያው የጦርነት ጊዜ እያሸነፍናቸው ነው” አሉ።