መሳፍንት 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ብንያማውያን፥ እስራኤላውያን ወደ ምጽጳ መውጣታቸውን ሰሙ፤ ከዚያም እስራኤላውያን፥ “ይህ ክፉ ድርጊት እንዴት እንደ ተፈጸመ እስቲ ንገሩን” ተባባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ብንያማውያን፣ እስራኤላውያን ወደ ምጽጳ መውጣታቸውን ሰሙ፤ ከዚያም እስራኤላውያን፣ “ይህ ክፉ ድርጊት እንዴት እንደ ተፈጸመ እስኪ ንገሩን?” ተባባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የብንያም ነገድ እስራኤላውያን በሙሉ በምጽጳ መሰብሰባቸውን ሰሙ። እስራኤላውያንም “ይህ ክፉ ሥራ የተፈጸመው እንዴት እንደ ሆነ ንገሩን!” አሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ልጆች የእስራኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእስራኤልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እንደምን እንደ ተደረገ ንገሩን” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምም ልጆች የእስራኤል ልጆች ወደ ምጽጳ እንደ ወጡ ሰሙ። የእስራኤልም ልጆች፦ ይህ ክፉ ነገር እንደምን እንደ ተደረገ ንገሩን አሉ። |
ባላጋራህ ለዳኛ፥ ዳኛውም ለሎሌው እንዳይሰጥህ ወደ እስር ቤት እንዳትገባ፤ ከባላጋራህ ጋር በመንገድ አብረኸው ስትሄድ ሳለህ ፈጥነህ ተስማማ፤
የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች ሁሉ ቁጥራቸው አራት መቶ ሺህ በሚሆን፥ ሰይፍ በሚመዙ እግረኞች ወታደሮች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ መካከል ተገኙ።