መሳፍንት 20:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ነገዶች ለመላው የብንያም ነገድ እንዲህ በማለት መልእክተኞች ላኩ፥ “በመካከላችሁ የተፈጸመው ይህ ክፉ ድርጊት ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ነገዶች ለመላው የብንያም ነገድ እንዲህ በማለት መልእክተኞች ላኩ፣ “በመካከላችሁ የተፈጸመው ይህ ክፉ ድርጊት ምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ነገዶች በመላው በብንያም ግዛት ተዘዋውረው እንዲህ የሚል ቃል የሚናገሩትን መልእክተኞች ላኩ፥ “ይህ የፈጸማችሁት ክፉ ነገር ምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ነገዶች፥ “በእናንተ መካከል የተደረገ ይህ ክፉ ነገር ምንድን ነው?” ብለው ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ ሰዎችን ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ነገዶች፦ በእናንተ መካከል የተደረገ ይህ ክፉ ነገር ምንድር ነው? አሁንም እንድንገድላቸው ከእስራኤልም ክፋትን እንድናርቅ በጊብዓ ውስጥ ያሉትን ምናምንቴዎቹን ሰዎች አውጥታችሁ ስጡን ብለው ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ ሰዎችን ላኩ። የብንያም ልጆች ግን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አልወደዱም። |
አሁንም እነርሱን ገድለን ይህን ክፉ ድርጊት ከእስራኤል እንድናስወግድ፥ እነዚያን የጊብዓን ነውረኞች አሳልፋችሁ ስጡን።” ብንያማውያን ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን አልሰሟቸውም ነበር፤
በዚህ ጊዜ ብንያማውያን፥ እስራኤላውያን ወደ ምጽጳ መውጣታቸውን ሰሙ፤ ከዚያም እስራኤላውያን፥ “ይህ ክፉ ድርጊት እንዴት እንደ ተፈጸመ እስቲ ንገሩን” ተባባሉ።