ከዚያም አቤሴሎም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ እኔ ‘አምኖንን፥ ምቱት’ በምላችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔው ስለሆንኩ አትፍሩ፤ ብርቱዎች ሁኑ፥ ጨከን በሉም” ብሎ አዘዛቸው።
መሳፍንት 19:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውየውም ከቁባቱና ከአገልጋዩ ጋር ለመሄድ በተነሣ ጊዜ፥ የልጅቱ አባት ዐማቱ “እነሆ ጊዜው እየመሸ ነው፤ እዚሁ እደሩ፤ ቀኑ እየተገባደደ ነው፤ እዚሁ አድራችሁ ተደሰቱ፤ ነገ ጠዋት ማልዳችሁ በመነሣት መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም ከቁባቱና ከአገልጋዩ ጋራ ለመሄድ በተነሣ ጊዜ፣ የልጅቱ አባት ዐማቱ “እነሆ ጊዜው እየመሸ ነው፤ እዚሁ ዕደሩ፤ ቀኑ እየተገባደደ ነው፤ እዚሁ ዐድራችሁ ተደሰቱ፤ ነገ ጧት ማልዳችሁ በመነሣት መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋዊውና ቊባቱ እንዲሁም አገልጋዩ ሆነው እንደገና ጒዞ ሲጀምሩ የልጅቱ አባት እንዲህ አለ፤ “ተመልከቱ! እነሆ ጊዜው መሽቶአል፤ ሌሊቱን እዚሁ ብታሳልፉ ይሻላል፤ አሁን ፈጥኖ ይጨልማል፤ እዚሁ ደስ ብሎአችሁ ዕደሩ፤ ነገ በማለዳ ተነሥታችሁ ጒዞ በመጀመር ወደ ቤታችሁ ትሄዳላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውዬውም ከዕቅብቱና ከብላቴናው ጋር ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱ አባት አማቱም፥ “እነሆ፥ መሽትዋል፤ ፀሐዩም ሊጠልቅ ደርሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚህም ተቀመጥ፤ ልብህም ደስ ይበለው፤ በጥዋትም መንገዳችሁን ትገሠግሣላችሁ፤ ወደ ቤትህም ትገባለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም ከቁባቱና ከአሽከሩ ጋር ለመሄድ በተነሣ ጊዜ የብላቴናይቱ አባት አማቱ፦ እነሆ፥ ቀኑ ተዋግዶአል፥ በዚህ እደሩ፥ እነሆ፥ ቀኑ ለማለፍ ተዋግዶአል፥ ልባችሁ ደስ እንዲለው በዚህ እደሩ፥ ነገም ወደ ቤታችሁ እንድትደርሱ ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለው። |
ከዚያም አቤሴሎም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ እኔ ‘አምኖንን፥ ምቱት’ በምላችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔው ስለሆንኩ አትፍሩ፤ ብርቱዎች ሁኑ፥ ጨከን በሉም” ብሎ አዘዛቸው።
ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ የቡስ ሄደ።
በአምስተኛውም ቀን ጠዋት ሌዋዊው ለመሄድ ሲነሣ፥ የልጂቱ አባት “ሰውነትህን አበርታ፤ ጥላው እስኪበርድም ድረስ በዚሁ ቈይ” አለው፤ ስለዚህ ሁለቱም አብረው በሉ።