መሳፍንት 19:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ወደ ቤቱ አስገብቶት ለአህዮቹ ገፈራ ሰጣቸው፤ እንግዶቹም እግራቸውን ታጠቡ፤ በሉ፤ ጠጡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወደ ቤቱ አስገብቶት ለአህዮቹ ገፈራ ሰጣቸው፤ እንግዶቹም እግራቸውን ታጠቡ፤ በሉ፤ ጠጡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወደ ቤት ወሰዳቸውና ለአህዮቹ ገፈራ መገበለት፤ እንግዶቹም እግራቸውን ታጥበው ራታቸው በሉም ጠጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤቱም አስገባው፤ ለአህዮቹም ገፈራ ጣለላቸው፤ እግራቸውንም ታጠቡ፤ በሉም፤ ጠጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቤቱም አስገባው፥ ለአህዮቹም ገፈራ ጣለላቸው፥ እግራቸውንም ታጠቡ፥ በሉም ጠጡም። |
ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው። የቤቱ አዛዥ ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገብቶ እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አቀረበላቸው፤ ለአህዮቻቸውም የሚበሉት ገፈራ ሰጣቸው።
ከዚያም ዳዊት ኦርዮንን፥ “በል እንግዲህ ወደ ቤትህ ወርደህ እግርህን ታጠብ” አለው። ኦርዮን ከቤተ መንግሥት ተሰናብቶ ወጣ፤ ንጉሡም የምግብ ስጦታ ላከለት።
ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጉርዋም አበሰች።
እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በበጎም ሥራ ሁሉ በመትጋት፥ በመልካም ሥራዎችዋ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
እርሷም ተነሥታ በግምባሯ በመደፋት እጅ ከነሣች በኋላ፥ “እነሆ፤ እኔ አገልጋይህ አንተን ለማገልገል፥ የጌታዬንም አገልጋዮች እግር ለማጠብ ዝግጁ ነኝ” አለች።