መሳፍንት 18:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሕፃናታቸውን፥ የከብቶቻቸውን መንጋና ሀብታቸውን ሁሉ ወደ ፊት በማስቀደም ተመልሰው ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ሕፃናታቸውን፣ የከብቶቻቸውን መንጋና ሀብታቸውን ሁሉ ወደ ፊት በማስቀደም ተመልሰው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ከፊት አስቀድመው ወደ ኋላ በመመለስ ጒዞአቸውን ቀጠሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ተመልሰው ሄዱ፤ ቤተ ሰቡን፥ ገንዘቡንና ሀብቱንም ሁሉ፥ በፊታቸው አድርገው ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ዞረው ሄዱ፥ ሕፃናቶችንና ከብቶችን ዕቃዎችንም በፊታቸው አደረጉ። |