መሳፍንት 16:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጋዛ ሰዎች፥ “ሳምሶን እዚህ ነው!” የሚል ወሬ ደረሳቸው፤ ስለዚህም ሰዎቹ ቦታውን ከበው፤ ሌሊቱን በሙሉ በከተማይቱ ቅጥር በር ላይ አድፍጠው ጠበቊት፤ “በማለዳ እንገድለዋለን” በማለትም ሌሊቱን በሙሉ እንዳደፈጡ አደሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋዛ ሰዎች፣ “ሳምሶን እዚህ ነው!” የሚል ወሬ ደረሳቸው፤ ስለዚህም ሰዎቹ ቦታውን ከብበው፤ ሌሊቱን በሙሉ በከተማዪቱ ቅጥር በር ላይ አድፍጠው ጠበቁት፤ “በማለዳ እንገድለዋለን” በማለትም ሌሊቱን በሙሉ እንዳደፈጡ ዐደሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጋዛም ሰዎች ሶምሶን በዚያ መኖሩን ሰምተው ያንን ቦታ በመክበብ በከተማይቱ በር ሌሊቱን ሙሉ ሲጠብቁት ዐደሩ፤ “እስኪነጋ ጠብቀን እንገድለዋለን” ብለው በማሰብ ሌሊቱን ሙሉ አደፈጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጋዛ ሰዎችም፥ “ሶምሶን ወደዚህ መጥቶአል” ብለው ነገሩአቸው፤ ከበቡትም። ሌሊቱንም ሁሉ በከተማዪቱ በር ሸመቁበት፥ “ማለዳ እንገድለዋለን” ብለውም ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋዛ ሰዎችም ሶምሶን ወደ ከተማ ውስጥ እንደ ገባ ሰሙ፥ ከበቡትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ በከተማይቱ በር ሸመቁበት፦ ማለዳ እንገድለዋለን ብለውም ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ። |
እንግዲህ አሁን እናንተ ከሸንጎው ጋር ሆናችሁ ስለ እርሱ አጥብቃችሁ እንደምትመረምሩ መስላችሁ ወደ እናንተ እንዲያወርደው ለሻለቃው አመልክቱት፤ እኛም ሳይቀርብ እንድንገድለው የተዘጋጀን ነን፤” አሉአቸው።
እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ ጌታ ጮኸ።
ነገር ግን ሳምሶን እዚያ የተኛው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ተነሥቶም የከተማይቱን ቅጥር በር ከሁለት መቃኖቸ ጋር መወርወሪያውንና ማያያዣውን ጭምር በሙሉ ነቅሎ በትከሻው ላይ ካደረገ በኋላ፥ በኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኰረብታ ጫፍ ድረስ ተሸክሞት ወጣ።
ሳኦልም የዳዊትን ቤት ከበው በማለዳ እንዲገድሉት ሰዎችን ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮል ግን፥ “ሕይወትህን ለማትረፍ በዚህች ሌሊት ካልሸሸህ፥ በነገው ቀን ትገደላለህ” ብላ አስጠነቀቀችው።
ሳኦል በተራራው በአንዱ በኩል ሆኖ ሲያሳድድ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ በተራራው በሌላ በኩል ከሳኦል ለማምለጥ ይጣደፉ ነበር። ሳኦልና ወታደሮቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ከበው ለመያዝ ተቃርበው ሳሉ፥