በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ስለዚህ የፍየል ጠቦት እንደሚገነጣጠል አንበሳውን ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጠለው፤ ያደርገውን ግን ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም ነበር።
መሳፍንት 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሴቲቱም ወረደ፤ ከእርሷም ጋር ተነጋገረ፤ እጅግም ወደዳት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ሴቲቱም ወረደ፤ ከርሷም ጋራ ተነጋገረ፤ እጅግም ወደዳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ወደ ሴቲቱ ሄዶ አነጋገራት፤ ወደዳትም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሂደውም ከሴቲቱ ጋር ተነጋገሩ፤ ሶምሶንንም በፊቱ ደስ አሰኘችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወርዶም ከሴቲቱ ጋር ተነጋገረ፥ እጅግም ደስ አሰኘችው። |
በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ስለዚህ የፍየል ጠቦት እንደሚገነጣጠል አንበሳውን ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጠለው፤ ያደርገውን ግን ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም ነበር።
ከጥቂት ቀን በኋላም ሊያገባት ተመለሰ፤ የአንበሳውንም በድን ለማየት ከመንገድ ዘወር አለ፤ በበድኑም ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮ ተመለከተ፤ ማርም ነበረበት፤