“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
መሳፍንት 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳምሶንም፥ “ከበላተኛው መብል፥ ከብርቱም ጣፋጭ ነገር ወጣ” አላቸው። እነርሱም እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንቈቅልሹን መፍታት አልቻሉም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳምሶንም፣ “ከበላተኛው መብል፣ ከብርቱም ጣፋጭ ነገር ወጣ” አላቸው። እነርሱም እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንቈቅልሹን መፍታት አልቻሉም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ከበላተኛው መብል ተገኘ፤ ከብርቱውም ጣፋጭ ነገር ወጣ” አላቸው። እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንቆቅልሹን መፍታት አልቻሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ከበላተኛ መብል ወጣ፤ ከብርቱም ጣፋጭ ወጣ” አላቸው። እስከ ሦስት ቀንም እንቆቅልሹን መፍታት አልቻሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ከበላተኛው ውስጥ መብል ወጣ፥ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ አላቸው። ሦስት ቀንም እንቈቅልሹን መተርጎም አልቻሉም። |
“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
ሰዎችም መጥተው እንዲህ በማለት ለኢዮሣፍጥ አወሩለት፦ “ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዐይን-ጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ይገኛሉ።”
ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፥ በዘበዙትም፥ ሁሉንም ለመሸከም አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።
እንቈቅልሹን ካልፈታችሁልኝ ግን ሠላሳ የቀጭን ፈትል በፍታ ቀሚስና ሠላሳውን የክት ልብስ እናንተ ትሰጡኛላችሁ።” እነርሱም፥ “በል እንቈቅልሽህን ንገረንና እንስማው” አሉት።
በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፥ “የእንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስቲ አግባቢልን፤ ያለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው እንዴ?” አሏት።