ያኢር በሠላሳ አህዮች የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ልጆቹም እስከ ዛሬ ድረስ የያኢር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች በገለዓድ ምድር ነበሯቸው።
መሳፍንት 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም በሰባ አህዮች ላይ የሚቀመጡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፤ በእስራኤልም ላይ ስምንት ዓመት ፈራጅ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በሰባ አህዮች ላይ የሚቀመጡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፤ በእስራኤልም ላይ ስምንት ዓመት ፈራጅ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓብዶን በሰባ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ የልጅ ልጆች ነበሩት፤ ዓብዶን ስምንት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርባም ልጆች፥ ሠላሳም የልጅ ልጆች ተወለዱለት፤ በሰባም የአህያ ግልገሎች ላይ ይቀመጡ ነበር። እስራኤልንም ስምንት ዓመት ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አርባም ልጆች ሠላሳም የልጅ ልጆች ነበሩት፥ በሰባም አህያ ግልገሎች ላይ ይቀመጡ ነበር። በእስራኤልም ላይ ስምንት ዓመት ፈረደ። |
ያኢር በሠላሳ አህዮች የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ልጆቹም እስከ ዛሬ ድረስ የያኢር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች በገለዓድ ምድር ነበሯቸው።