እነርሱም፥ “ከአሞናውያን ጋር መዋጋት እንችል ዘንድ መጥተህ ምራን” አሉት።
እነርሱም ዮፍታሔን፣ “ከአሞናውያን ጋራ መዋጋት እንችል ዘንድ መጥተህ ምራን” አሉት።
ዮፍታሔንም፦ “ዐሞናውያንን መውጋት እንችል ዘንድ መጥተህ መሪያችን ሁን” አሉት።
ዮፍታሔንም፥ “ና፥ ከአሞን ልጆች ጋር እንድንዋጋ መስፍን ሁነን” አሉት።
ዮፍታሔንም፦ ና፥ ከአሞን ልጆች ጋር እንድንዋጋ አለቃችን ሁን አሉት።
ሰውም በአባቱ ቤት ከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፤ “አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ ይህንንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል።
አሞናውያን ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በገለዓድ በሰፈሩ ጊዜ፥ እስራኤላውያንም እንደዚሁ ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ።
የገለዓድ አለቆች ዮፍታሔን ለማምጣት ወደ ጦብ ምድር ሄዱ።
ዮፍታሔም፥ “ምነው ጠልታችሁኝ ከአባቴ ቤት አሳዳችሁኝ አልነበረምን? ታዲያ አሁን ችግር ሲገጥማችሁ ነው የምትፈልጉኝ?” አላቸው።