መሳፍንት 11:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “በይ ሂጂ” ብሎ ለሁለት ወር አሰናበታት፤ እርሷም ከእንግዲህ ባል ስለማታገባ ከልጃገረድ ጓደኞቿ ጋር ወደ ተራሮች ሄደው አለቀሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “በይ ሂጂ” ብሎ ለሁለት ወር አሰናበታት፤ እርሷም ከእንግዲህ ባል ስለማታገባ ከልጃገረድ ጓደኞቿ ጋራ ወደ ተራሮች ሄደው አለቀሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንድትሄድ ፈቅዶ ለሁለት ወር አሰናበታት፤ እርስዋና ጓደኞችዋም ወደ ተራራዎች ወጡ፤ ከዚያም ባል አግብታ ልጆች የማትወልድ በመሆንዋ አለቀሱላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ሂጂ” አለ። ሁለት ወርም አሰናበታት፤ ከባልንጀሮችዋም ጋር ሄደች፤ በተራሮችም ላይ ለድንግልናዋ አለቀሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ሂጂ አለ። ሁለት ወርም አሰናበታት፥ ከባልንጀሮችዋም ጋር ሄደች፥ በተራሮችም ላይ ለድንግልናዋ አለቀሰች። |
ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ፤ ከእንግዲህ ባል ስለማላገባ ከባልንጀሮቼ ጋር ወደ ተራሮች ወጥቼ እየዞርሁ ሁለት ወር እንዳለቅስ አሰናብተኝ።”