መሳፍንት 11:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴዎን ግን በግዛቱ እንዲያልፍ ለመፍቀድ እስራኤልን አላመነውም፤ ሠራዊቱንም ሰብስቦ በያሃጽ ከሰፈረ በኋላ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴዎን ግን በግዛቱ እንዲያልፍ ለመፍቀድ እስራኤልን አላመነውም፤ ሰራዊቱንም ሰብስቦ በያሀጽ ከሰፈረ በኋላ ከእስራኤል ጋራ ተዋጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሲሖን ግን እስራኤላውያን አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም መላ ሠራዊቱን ሰብስቦ በያሐጽ በመስፈር ከእስራኤል ጋር ተዋጋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ በኢያሴርም ሰፈረ፤ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም ነበር፥ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ በያሀጽም ሰፈረ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። |
“ከዚያም እስራኤል በሐሴቦን ወዳለው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞች ልኮ፥ ‘ወደ ገዛ ስፍራችን ለመሄድ በአገርህ እንዳልፍ ፍቀድልኝ’ አለው።
“ከዚያም የእስራኤል አምላክ ጌታ ሴዎንንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤” አሸነፏቸውም፤ እስራኤልም በዚያ አገር የሚኖሩትን የአሞራውያንን ምድር በሙሉ ወረሰ፤