ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ የደረሰብንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤
መሳፍንት 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዮፍታሔ ወደ አሞናውያን ንጉሥ፥ “ከእኔ ጋር ምን ጠብ ቢኖርህ ነው መጥተህ አገሬን የወጋኸው?” በማለት መልእክተኞች ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዮፍታሔ ወደ አሞናውያን ንጉሥ፣ “ከእኔ ጋራ ምን ጠብ ቢኖርህ ነው መጥተህ አገሬን የወጋኸው?” በማለት መልእክተኞች ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዮፍታሔ ወደ ዐሞን ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ “ከእኛ ጋር የተጣላህበት ምክንያት ምንድን ነው? አገራችንንስ የወረርከው ለምንድነው?” ብለው እንዲጠይቁት አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ “ሀገሬን ለመውጋት ወደ እኔ የምትመጣ አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ?” ብሎ መልእክተኞችን ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፦ አገሬን ለመውጋት ወደ እኔ የምትመጣ አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ብሎ መልክተኞችን ላከ። |
ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ የደረሰብንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤
ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ አለቆች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም በላያቸው ላይ አለቃና አዛዥ አደረጉት፤ ዮፍታሔም የተናገረውን ቃል ሁሉ ምጽጳ ላይ በጌታ ፊት ደገመው።
የአሞናውያንም ንጉሥ ለዮፍታሔ መልእክተኞች፥ “ይህን ያደረግሁት እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ በአርኖንና በያቦቅ ወንዞች መካከል ያለውንና እስከ ዮርዳኖስ ያለውን አገሬን ስለ ወሰዱብኝ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” አላቸው።
ዮፍታሔም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከአሞናውያን ጋር ከፍተኛ ትግል ገጥመን በነበረበት ጊዜ ጠርቼያችሁ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም፤