መሳፍንት 1:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካሌብም ትንሽ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ዖትኒኤል ያዛት፥ ልጁንም ዓክሳን ዳረለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳንን ዳረለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የካሌብ ታናሽ ወንድም የቀናዝ ልጅ ዖትኒኤል ከተማይቱን ቀድሞ ያዘ፤ ስለዚህም ካሌብ ሴት ልጁን ዓክሳን ዳረለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካሌብም ትንሽ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፤ ሚስትም ትሆነው ዘንድ ልጁን ዓስካን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካሌብም ትንሽ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፥ ልጁንም ዓክሳን አጋባው። |