ከእርሷ በበላችሁ ቀን ዐይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ፥ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።”
ይሁዳ 1:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም በተመሳሳይ ሁኔታ እነዚህ ሕልመኞች ሥጋን ያረክሳሉ፥ ጌትነትን ይቃወማሉ፥ ክብር ያላቸውንም ይሳደባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታ እነዚህ ሕልም ዐላሚዎች የገዛ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ሥልጣንን አይቀበሉም፤ በሰማይ ክብር ያላቸውንም ፍጥረታት ይሳደባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እነዚህ ሰዎች በሕልማቸው እየተመሩ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ለባለ ሥልጣኖችም አይታዘዙም፤ በሰማይ ክብር ያላቸውንም ይሳደባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ጌትነትንም ይጥላሉ፤ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ ጌትነትንም ይጥላሉ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ። |
ከእርሷ በበላችሁ ቀን ዐይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ፥ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።”
የሰማይ ወፍ ቃሉን ይወስደዋልና፥ ባለ ክንፎችም ነገሩን ይናገራሉና በልብህ አሳብ እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትስደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትስደብ።
በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ ጌታም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችሁታል፤ በጌታም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?”
ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ ይኼውም እናንተ ናችሁ።
ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለሐሰተኞችም፥ በውሸትም ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው።
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። እነርሱ እንደሚጠየቁበት አድርገው ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ፤ ይህንንም በደስታ እንጂ በኀዘን እንዳያደርጉት፥ አለበለዚያ አይጠቅማችሁም።