ይሁዳ 1:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚጠራጠሩትን ምሕረት አድርጉላቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተጠራጣሪ ለሆኑት ራሩላቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚጠራጠሩ ሰዎች ርኅራኄ አድርጉላቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፤ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ |
ወንድሞች ሆይ! ሰው ማንኛውንም ኃጢአት አድርጎ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ዓይነቱን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።