La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ጊዜም ጌታ ኢያሱን፦ “የባልጩት መቁረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “የባልጩት መቍረጫ አዘጋጅተህ፣ ያልተገረዙትን እስራኤላውያንን ለሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን “ከባልጩት የተሠራ መቊረጫ አዘጋጅተህ እስራኤላውያንን እንደገና ግረዛቸው” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን፥ “ከሻፎ ድን​ጋይ የባ​ል​ጩት መቍ​ረጫ ሠር​ተህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዳግ​መኛ ግረ​ዛ​ቸው” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ኢያሱን፦ የባልጩት መቁረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው አለው።

Ver Capítulo



ኢያሱ 5:2
8 Referencias Cruzadas  

ፂፖራም ባልጩት ወሰደች፥ የልጇንም ሸለፈት ገረዘች፥ እግሩንም ነክታ፦ “አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ” አለች።


ነገር ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፤ መገረዝም በመንፈስ የሆነ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በፊደል አይደለም፤ ምስጋናውም ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።


ሳይገረዝም በእምነቱ ባገኘው የጽድቅ ማኅተም፥ መገረዝን እንደ ምልክት ተቀበለ፤ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ፥ ለእነርሱም ጽድቅ ሆኖ እንዲቆጠርላቸው አባት ነውና፤


እንግዲህ እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።


ጌታ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወደው፥ በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህ ጌታ የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።


በክርስቶስ መገረዝ የሥጋዊውን አካል በመግፈፍ በሰው እጅ ባልተከናወነ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ፤


ኢያሱም የባልጩት መቁረጫ ሠርቶ የግርዛት ኮረብታ በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ልጆች ገረዘ።