La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 19:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህ ለዳን ነገድ ርስት ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮች ነበሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ እነዚህ ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች የዳን ልጆች በየወገናቸው ርስት ናቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዳን ልጆ​ችም ሄደው ለኪ​ስን መቱ​አት፤ ከተ​ማ​ቸ​ው​ንም ያዟት፤ በሰ​ይ​ፍም መቱ​አት። በው​ስ​ጥ​ዋም ተቀ​መጡ። ስሟ​ንም በአ​ባ​ታ​ቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩ​አት። አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም በኤ​ዶ​ምና በሰ​ላ​ሚን ለመ​ኖር ቀጠሉ። የኤ​ፍ​ሬ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ በረ​ታች። ገባ​ሪ​ዎ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

Ver Capítulo



ኢያሱ 19:48
3 Referencias Cruzadas  

የነገዶቹ ስም ይህ ነው። ከሰሜን ወሰን በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ በደማስቆም ድንበር ባለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ካለው ከሰሜን ድንበር ይጀምራል። ወርዳቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።


የዳንም ልጆች ግዛታቸውን መቆጣጠር ባለልቻሉ ጊዜ ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፤ ሌሼም የነበረውን ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት።


ምድሩንም ሁሉ በየግዛቱ ርስት እንዲሆን አከፋፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።