La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 19:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት-ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድንበሩ በአዝኖት ታቦር ያልፍና ወደ ምዕራብ በመታጠፍ ሑቆቅ ላይ ይቆማል፤ ይኸው ድንበር በደቡብ ዛብሎንን፣ በምዕራብ አሴርን፣ በምሥራቅ ዮርዳኖስን ይነካል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ ድንበሩ በምዕራብ በኩል ወደ አዝኖትታቦር ይታጠፋል፤ ከዚያም ወደ ሁቆቅ ይሄዳል፤ በደቡብ በኩል ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል አሴርን፥ በስተምሥራቅ ዮርዳኖስ የሚያዋስነው ይሁዳን ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድን​በ​ሩም ወደ ምዕ​ራብ ወደ አዝ​ኖ​ት​ታ​ቦር ይዞ​ራል፤ ከዚ​ያም ወደ ያቃና ይወ​ጣል፤ ከዚ​ያም በደ​ቡብ በኩል ወደ ዛብ​ሎን፤ በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም በፀ​ሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደ​ር​ሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፥ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 19:34
5 Referencias Cruzadas  

ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በሞገስ ጠግቧል፥ የጌታንም በረከት ተሞልቶአል፥ ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል።”


ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎትታቦር ዳርቻ ዞረ፤ ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ፤


ድንበሩም ወደ ታቦርና ወደ ሻሕጹማ፥ ወደ ቤት-ሳሚስ ደረሰ፥ የድንበራቸውም መጨረሻ ዮርዳኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ በጸዕነኒም ካለው ከባሉጥ ዛፍ፥ ከአዳሚ-ኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መጨረሻውም በዮርዳኖስ ነበረ።


የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥