ኢያሱ 19:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ በጸዕነኒም ካለው ከባሉጥ ዛፍ፥ ከአዳሚ-ኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መጨረሻውም በዮርዳኖስ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንበራቸውም ከሔሌፍና በጻዕናይም ካለው ከትልቁ የወርካ ዛፍ ይነሣና በአዳሚኔቄብና በየብኒኤል ዐልፎ ወደ ለቁም በመምጣት ዮርዳኖስ ላይ ይቆማል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንበሩም ከሔሌፍ በመነሣት በአዳሚኔቄብና በያሚኒያ በኩል መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ እስከ ላቁም ድረስ እስከ ዳዕናኒም ወርካ ይዘልቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበራቸውም ከመሐላም፥ ከሞላም፥ ከቤሴሜይን፥ ከአርሜ፥ ከናቦቅና፥ ከኢያፍታሜን እስከ ይዳም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ከጸዕነኒም ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፥ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ። |
ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት-ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።
በዚያን ጊዜ ቄናዊው ሔቤር፥ ዐማች የአባብ ልጆች ከሆኑት ከሌሎቹ ቄናውያን ተለይቶ በቃዴስ አጠገብ ጻዕናይም ከተባለ ቦታ ከሚገኘው ባሉጥ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተክሎ ነበር።