ዮናስ 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነነዌ ሁሉ ይህንን አዋጅ አስነገረ፦ በንጉሡና በመኳንንቱ ትእዛዝ መሠረት፥ ሰውም ሆነ እንስሳ፥ ከብትም ሆነ በግ አንዳች አይቅመሱ፤ አይሰማሩ፥ ውኃም አይጠጡ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እንዲህ ሲል በነነዌ ዐዋጅ አስነገረ፤ “ከንጉሡና ከመሳፍንቱ የወጣ ዐዋጅ፤ “ማንም ሰው ወይም እንስሳ፣ የከብት መንጋም ሆነ የበግ መንጋ፣ ምንም ነገር አይቅመስ፤ አይብላ፤ ውሃም አይጠጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለነነዌም ሕዝብ እንዲህ ሲል ዐዋጅ አስነገረ፥ “ከንጉሡና ከመኳንንቱ በተላለፈው ትእዛዝ መሠረት፥ ማንም ሰው ወይም እንስሳ፥ የከብትም ሆነ የበግ መንጋ አንዳች ምግብ አይቅመሱ፤ ውሃም አይጠጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐዋጅም አስነገረ፤ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ፥ “ሰዎችና እንስሶች፥ ላሞችና በጎች አንዳች አይቅመሱ፤ አይሰማሩም፤ ውኃንም አይጠጡ፤ |
በአምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንድንለምን በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።