አይሁድም “ገና አምሳ ዓመት አልሞላህም፤ አብርሃምን አይተሃልን?” አሉት።
አይሁድም፣ “ገና ዐምሳ ዓመት ያልሞላህ፣ አንተ አብርሃምን አይተሃል!” አሉት።
በዚህ ጊዜ አይሁድ፥ “አንተ ገና ኀምሳ ዓመት እንኳ አልሆነህም፤ ታዲያ እንዴት አብርሃምን አየሁ ትላለህ?” አሉት።
አይሁድም፥ “ገና አምሳ ዓመት ያልሞላህ እንዴት አብርሃምን አየህ?” አሉት።
አይሁድም፦ “ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን?” አሉት።
አይሁድም “አንተ ማን ነህ?” ብለው ለመጠየቅ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
ኢየሱስም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ፤” አላቸው።