ዮሐንስ 8:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያም ለዘለዓለም በቤት አይኖርም፤ ልጁ ለዘለዓለም ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሪያ ለዘለቄታ በቤተ ሰቡ ውስጥ አይኖርም፤ ልጅ ግን ምን ጊዜም በቤት ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያ ሁልጊዜ በቤት ውስጥ አይኖርም፤ ልጅ ግን ሁልጊዜ በቤት ውስጥ ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባርያ ዘወትር በቤት አይኖርም፤ ልጅ ግን ለዘለዓለም ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባርያም ለዘላለም በቤት አይኖርም፤ ልጁ ለዘላለም ይኖራል። |
ነገር ግን ከባርያዎቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነጻነት ዓመት ድረሰ ለእርሱ ይሁን፥ ከዚያም በኋላ ለመስፍኑ ይመለስለት፤ ርስቱ ለልጆቹ ብቻ ይሁን።