ዮሐንስ 8:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድም “‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ ማለቱ እራሱን ሊገድል ይሆን?” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም፣ “ ‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ ያለው ራሱን ሊገድል ይሆን?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ ባለሥልጣኖችም “ ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ ማለቱ ራሱን ሊገድል ይሆን?” ተባባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም፥ “እኔ ወደምሄድበት እናንተ መምጣት አትችሉም የሚለን እርሱ ራሱን ይገድል ይሆን? እንጃ!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድም፦ “እኔ ወደ ምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም ማለቱ ራሱን ይገድላልን? እንጃ” አሉ። |
አይሁድም እንዲህ ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ “እኛ እንዳናገኘው ይህ ሰው ወዴት ሊሄድ ነው? በግሪክ ሰዎች መካከል ተበትነው ወደሚኖሩት ሄዶ የግሪክን ሰዎች ሊያስተምር ነውን?
አይሁድ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም እንኳን ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም፤’ ትላለህ።