ዮሐንስ 4:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደመጣ ሰምቶ፥ ልጁ ሊሞት ስለ ቀረበ፥ ወደ እርሱ ሄደ፤ ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሰው ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መምጣቱን በሰማ ጊዜ፣ ወደ እርሱ ሄደና በሞት አፋፍ ላይ የነበረውን ልጁን መጥቶ እንዲፈውስለት ለመነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ምድር ወደ ገሊላ መምጣቱን ሰምቶ ወደ እርሱ ሄደ፤ ወደ ቅፍርናሆም እንዲወርድና በጠና ታሞ ሊሞት የተቃረበውን ልጁን እንዲፈውስለት ኢየሱስን ለመነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ሄደ፤ ሊሞት ቀርቦ ነበርና ወርዶ ልጁን ያድንለት ዘንድ ለመነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ ሰምቶ ልጁ ሊሞት ስላለው ወደ እርሱ ሄደ ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው። |
ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ናትና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው፥ ወደ እነርሱ ከመምጣት እንዳይዘገይ እየለመኑ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ።