ዮሐንስ 4:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱ “ክርስቶስ የሚባል መሢሕ እንደሚመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል፤” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም፣ “ክርስቶስ የተባለ መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ይነግረናል” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትዮዋም “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ይነግረናል” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም፥ “ክርስቶስ የሚሉት መሲሕ እንደሚመጣ እናውቃለን፤ እርሱም በሚመጣ ጊዜ ሁሉን ይነግረናል” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱ፦ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው። |
ሴቲቱንም “አሁን የምናምነው በቃልሽ ምክንያት አይደለም፤ እኛ እራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱ በእውነት የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን፤” ይሉአት ነበር።