ዮሐንስ 20:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መግደላዊት ማርያም ሄደችና ጌታን እንዳየችው፥ ይህንንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መግደላዊት ማርያምም፣ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥታ፣ “ጌታን እኮ አየሁት!” አለች፤ እርሱ ያላትንም ነገረቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ መግደላዊት ማርያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሄዳ ጌታን እንዳየችና እርሱም ምን እንዳላት ነገረቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማርያም መግደላዊትም ሄደች፤ ጌታን እንደ አየች፥ ይህንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መግደላዊት ማርያም መጥታ ጌታን እንዳየች ይህንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች። |
ይህንንም ለሐዋርያት የነገሩአቸው መግደላዊት ማርያምና ዮሐና፥ የያዕቆብም እናት ማርያም፥ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የነበሩ ሌሎች ሴቶች ነበሩበት።