La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 20:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁለት ነጭ ልብስ የለበሱ መላእክትም፥ የኢየሱስን ሥጋ አስተኝተውበት በነበረበት ስፍራ፥ አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የኢየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ፣ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት አንዱ በራስጌ ሌላው በግርጌ ተቀምጠው አየች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኢየሱስ አስከሬን በነበረበት ስፍራ ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት አንዱ በራስጌ፥ አንዱ በግርጌ ተቀምጠው አየች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁለት መላ​እ​ክ​ት​ንም ነጭ ልብስ ለብ​ሰው የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ሥጋ በነ​በ​ረ​በት ቦታ አንዱ በራ​ስጌ፥ አን​ዱም በግ​ርጌ ተቀ​ም​ጠው አየች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 20:12
10 Referencias Cruzadas  

መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጽናጽልና በገና መሰንቆም ይዘው በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ መለከት የሚነፉ ካህናት ነበሩ፤


በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።


እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤


ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር በሰርዴስ አሉ፤ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። እንዲህም አለኝም፦ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሶቻቸውንም አጥበው በበጉ ደም አንጽተዋል።