La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም “ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው፤” አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስ አገልጋዮቹን፣ “ጋኖቹን ውሃ ሙሏቸው” አላቸው፤ እነርሱም፣ ጋኖቹን እስከ አፋቸው ሞሏቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስ አገልጋዮቹን “ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው” አላቸው፤ እነርሱም እስከ አፋቸው ሞሉአቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ጋኖ​ቹን ውኃ ሙሉ​አ​ቸው” አላ​ቸው፤ እስከ አፋ​ቸ​ውም እስከ ላይ ሞሉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 2:7
12 Referencias Cruzadas  

ኤልያስም እንዲህ አላት፤ “አይዞሽ አትጨነቂ! ሄደሽ ምግብሽን አዘጋጂ፤ አስቀድመሽ ግን ከዚያችው ካለችሽ ዱቄት ለእኔ ትንሽ እንጐቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ የቀረውንም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪው፤


የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም፤” አለችው።


እናቱም ለአገልጋዮቹ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፤” አለቻቸው።


አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።


“አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት፤” አላቸው፤ ሰጡትም።