La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአይሁድ የመንጻት ሥርዐት መሠረት፣ ከሰባ ዐምስት እስከ አንድ መቶ ዐሥራ ዐምስት ሊትር የሚይዙ ከድንጋይ የተሠሩ ስድስት ጋኖች በዚያ ነበሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አይሁድ የመንጻት ሥርዓት ስለ ነበራቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱ ጋን ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ውሃ ለመያዝ ይችል ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም እንደ አይ​ሁድ ልማድ የሚ​ያ​ነ​ጹ​ባ​ቸው ስድ​ስት የድ​ን​ጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁለት ወይም ሦስት እን​ስራ ይይዙ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 2:6
9 Referencias Cruzadas  

እርሱም ‘መቶ ማድጋ ዘይት’ አለ። ‘የጽሑፍ ማስረጃህን እንካ፥ ፈጥነህም ተቀምጠና ኀምሳ ብለህ ጻፍ፤’ አለው።


ኢየሱስም “ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው፤” አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።


በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከልም ስለ ማንጻት ሥርዓት ክርክር ተነሣ።


ከውሃ መታጠብ ጋር በቃሉ አንጽቶ እንዲቀድሳት፥


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤


ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ነው።


ነገር ግን ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶች የሚውሉ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ስለ ሆኑ፥ እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ ናቸው።


እያንዳንዱን የሕግ ትእዛዝ በሙሴ ለሕዝቡ ከተነገረ በኋላ የጥጆችን ደም ከውሃ፥ ከቀይ የበግ ጠጒርና ከሂሶጵ ጋር ወስዶ፥ በመጽሐፉና በሕዝቡ ላይ ረጨው፤