ዮሐንስ 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአይሁድ ፋሲካም እንደ ተቃረበ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ ፋሲካ በዓል ቀርቦ ስለ ነበር ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአይሁድም የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። |
ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችን ወንበሮች ገለበጠ፤
ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፥ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያስወጣ ጀመር። የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ ገለባበጠ፤
ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።
“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ በቂጣ በዓል፥ በመከርንና በዳስ በዓል፥ በአምላክህ በጌታ ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፥ በጌታም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ።