እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ የተሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፥ ቢልቃጡንም ሰብራ ሽቱውን በራሱ ላይ አርከፈከፈችው።
ዮሐንስ 11:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማርያም ጌታን ሽቱ የቀባችው፥ እግሩንም በጠጉርዋ ያበሰችው ስትሆን፤ የታመመውም አልዓዛር ወንድምዋ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህች ወንድሟ አልዓዛር የታመመባት ማርያም፣ ጌታን ሽቱ ቀብታ እግሮቹን በጠጕሯ ያበሰችው ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህች ማርያም የጌታን እግር ሽቶ የቀባችውና በጠጒርዋ ያበሰችው ናት፤ የታመመውም አልዓዛር የእርስዋ ወንድም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማርያም ግን ጌታችንን ሽቱ የቀባችው፥ እግሩንም በጠጕርዋ ያሸችው ናት፤ ወንድምዋ አልዓዛርም ታሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር። |
እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ የተሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፥ ቢልቃጡንም ሰብራ ሽቱውን በራሱ ላይ አርከፈከፈችው።
ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቶ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጉርዋም አበሰቻችው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።