ዮሐንስ 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቢታንያም ዐሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ለኢየሩሳሌም ቅርብ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቢታንያ ከኢየሩሳሌም ዐሥራ ዐምስት ምዕራፍ ያህል ትርቅ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቢታንያ ከኢየሩሳሌም የምትርቀው ሦስት ኪሎ ሜትር ያኽል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቢታንያም ለኢየሩሳሌም ዐሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ቅርብ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቢታንያም አሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ለኢየሩሳሌም ቅርብ ነበረች። |
የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስና እስከ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ድረስ የሚርቅ ደም ከመጥመቂያው ወጣ።
ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፤ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት፤ ሁለት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ሜትር ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።