ደቀ መዛሙርቱም “ጌታ ሆይ! ተኝቶ እንደ ሆነስ ይድናል፤” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱም፣ “ጌታ ሆይ፤ ተኝቶ ከሆነስ ይድናል” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱም “ጌታ ሆይ! አንቀላፍቶስ ከሆነ ይሻለዋል ማለት ነው” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱም፥ “አቤቱ፥ ከተኛስ ይነቃል፤ ይድናልም” አሉት።
እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ ተኝቶስ እንደ ሆነ ይድናል” አሉት።
“ልጅቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ዞር በሉ፤” አላቸው። እነርሱ ግን ሳቁበት።
ይህንንም ከተናገረ በኋላ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ፤” አላቸው።
ኢየሱስ ግን ስለ ሞቱ ነበር የተናገረው፤ እነርሱ ግን ስለ እንቅልፍ የተናገረ መሰላቸው።